የሩሲያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በኩርስክ ክልል የዩክሬን ወታደሮች ሽንፈትን በተመለከተ ካቀረቡት ሪፖርት ዋና ዋና ነጥቦች፦
🔹የጄራሲሞቭ ቁልፍ መግለጫዎች፦
◾️ በኩርስክ የገቡትን የዩክሬን ኃይሎች ለማስወጣት የተካሄደው ዘመቻ ተጠናቋል። በክልሉ የመጨረሻው ጎርናል መንደር ዛሬ ቅዳሜ ነፃ ወጥቷል።
▪️ በኩርስክ ነፃ በወጡ አካባቢዎች ለመደበቅ እየሞከሩ ያሉትን የዩክሬን የጦር ኃይል ወታደሮች ለመለየት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።
▪️ የዩክሬን የጦር ኃይሎች በኩርስክ ከ76 ሺህ በላይ ወታደሮቹን በሞትና በጉዳት አጥቷል።
▪️ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ጦር ጋር በመሆን በጀግንነት ተዋግተዋል።
▪️ በሱሚ ክልል የፀጥታ ቀጣና ማቋቋም ቀጥሏል። አራት መንደሮች ነፃ የወጡ ሲሆን ከ90 ካሬ ኪ.ሜ በላይ መሬት በቁጥጥር ሥር ውሏል።
▪️ በኩርስክ የሚገኙ 19 መንደሮች ሙሉ በሙሉ ከፈንጂዎች ነጻ ሆነዋል።
🔹የፑቲን ቁልፍ መግለጫዎች፦
▪️ በኩርስክ የጠላት ሙሉ ሽንፈት በግንባሩ ሌሎች ወሳኝ ቦታዎች የሩሲያ የጦር ኃይሎች በቀጣይነት ስኬታማ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል።
▪️ የኪዬቭ አገዛዝ "ቁማር" ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።
▪️ የኩርስክ ነፃ መውጣት የኪዬቭን ኒዮ-ናዚ አገዛዝ ሽንፈት ያፋጥናል።
▪️ ፑቲን በኩርስክ ውጤታማ የነበሩትን የሩሲያ ጦር ክፍሎችን አመስግነዋል።
▪️ ኩርስክን ነፃ ላወጡ የሩሲያ ወታደሮች ጀግንነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲
መተግበሪያ | 👉
X ላይ ይከተሉን