ለሲኒየር የህክምና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የሰልጥኖ አሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ስልጠናው በውጊያ ወቅት የሚያጋጥሙ ጉዳቶች በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ያለመ የሰልጥኖ አሰልጣኞች ስልጠና ነው።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዛዥ ኮሎኔል በላቸው ካሳዬ ፣ ጤና ዋና መምሪያው የሰራዊቱን የጤና አገልግሎት ለማሳደግ በየዘርፉ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችን ለማፍራትና ለማብቃት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ስልጠናው ሲኒየር የህክምና ባለሙያዎች መሰጠቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት አዛዡ በውጊያ ወቅት የሚያጋጥሙ ጉዳቶችን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ መሆኑን ገልፀዋል።
በሰራዊቱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ እያገለገሉ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን ልምዶች በመቀመር ለትውልዱ መማሪያነት ማዋል እንደሚገባቸውም ገልፀዋል።
ሰልጣኞች የሰራዊት የህክምና ባለሙያዎችን በማብቃትና አቅማቸውን በመጨመር የሰራዊታችንን ጤንነት በማረጋገጥና ለግዳጅ ውጤታማነት የበኩላቸውን የመወጣት ተግባራቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል ።
የስልጠና ሪፖርት ያቀረቡት በጦር ሀይሎች ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስልጠናና ምርምር ዳይሬክተር ኮሎኔል ዶክተር አሰማ ተፈራ ፣ ሰልጣኞቹ በዘርፉ የረጅም ጊዜ የስራ ልምድና ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸው መሆኑንና በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የመጣው የህክምና ዘርፍ ላይ ያላቸውን አቅም የጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።
በስልጠናው የተገኙ ልምዶችን በተግባር በማዋል በውጊያ ወቅት የሚያጋጥሙ ጉዳቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ የሚያስችል አለም አቀፍ ልምዶች የተካተቱበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ስልጠናነው 68 ፐርሰንት በተግባር 32 ፐርሰንት በንድፈ ሀሳብ መሰጡቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ ሰልጣኞች ከሰማንያ በላይ ነጥብ ማስመዝገባቸው በምዘና መረጋገጡን ገልፀዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው አዳዲስ ልምዶችን ማግኘታቸው በዘርፉ ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ለመቀነስ አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።
በስልጠናው ባገኙት ዕውቀትም በሙያው ከማገልገል ባለፈ ከህክምና ባለሙያዎች በተጨማሪ ሁሉም የሰራዊቱ አባላት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ስልጠናው የጤና ሚኒስቴር ከጦር ሀይሎች ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ አባቱ ወልደማርያም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official